10. መከራን ከዐይኔ ይሰውር ዘንድ፣የእናቴን ማሕፀን ደጅ በላዬ አልዘጋምና።
11. “ምነው ገና ስወለድ በጠፋሁ!ምነው ከማሕፀን ስወጣ በሞትሁ!
12. የሚቀበሉኝ ጒልበቶች፤የሚያጠቡኝ ጡቶች ለምን ተገኙ?
13. ይህን ጊዜ በሰላም በተኛሁ፣አንቀላፍቼም ባረፍሁ ነበር፤
14. አሁን ፈርሶ የሚታየውን ስፍራ ለራሳቸው ካሠሩት፣ከምድር ነገሥታትና ከአማካሪዎች ጋር፣
15. ቤታቸውን በብር ከሞሉ፣ወርቅም ከነበራቸው ገዦች ጋር ባረፍሁ ነበር።
16. ወይም እንደ ተቀበረ ጭንጋፍ፣ብርሃንም እንዳላየ ሕፃን በሆንሁ ነበር።
17. በዚያ ክፉዎች ማወካቸውን ይተዋሉ፤ደካሞችም በዚያ ያርፋሉ፤
18. ምርኮኞች እንደ ልባቸው ይቀመጣሉ፤ከእንግዲህም የአስጨናቂዎቻቸውን ጩኸት አይሰሙም።
19. ትንሹም ትልቁም በዚያ ይገኛል፤ባሪያው ከጌታው ነጻ ወጥቶአል።
20. “በመከራ ላሉት ብርሃን፣ነፍሳቸው ለተማረረች ሕይወት ለምን ተሰጠ?
21. ሞትን በጒጒት ለሚጠብቁና ለማያገኙት፣ከተሰወረ ሀብት ይልቅ ለሚሹት፣
22. ወደ መቃብር ሲቃረቡ ደስ እያላቸው፣በሐሤት ለሚሞሉ ሕይወት ለምን ተሰጠ?