1. ከዚህ በኋላ፣ ኢዮብ አፉን ከፍቶ የተወለደበትን ቀን ረገመ፤
2. እንዲህም አለ፤
3. “የተወለድሁበት ቀን ይጥፋ፣‘ወንድ ልጅ ተፀነሰ’ የተባለበት ሌሊት።
4. ያ ቀን ጨለማ ይሁን፤እግዚአብሔር ከላይ አይመልከተው፤ብርሃንም አይብራበት።
5. ጨለማና የሞት ጥላ ይውረሱት፤ደመናም በላዩ ላይ ይረፍ፤ብርሃኑን ጽልመት ይዋጠው።
6. ያ ሌሊት በድቅድቅ ጨለማ ይያዝ፤ከዓመቱ ቀናት ጋር አይቈጠር፤ከወራቱ በአንዱም ውስጥ አይግባ።