ኢዮብ 29:7-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. “ወደ ከተማዪቱ በር ብቅ ባልሁ ጊዜ፣በአደባባይዋም በወንበር በተቀመጥሁ ጊዜ፣

8. ጐበዛዝት አይተውኝ ገለል ይሉ፣ሽማግሌዎችም ተነሥተው ይቆሙ ነበር።

9. የሰፈሩ ታላላቅ ሰዎች ከመናገር ይቈጠቡ፣እጃቸውንም በአፋቸው ላይ ይጭኑ ነበር፤

10. የመኳንንት ድምፅ ጸጥ ይል፣ምላሳቸውም ከላንቃቸው ጋር ይጣበቅ ነበር፤

11. የሰሙኝ ሁሉ ያሞጋግሱኝ፣ያዩኝም ያመሰግኑኝ ነበር፤

12. ለርዳታ የሚጮኸውን ችግረኛ፣ድኻ ዐደጉንም ታድጌአለሁና።

13. በሞት አፋፍ ላይ የነበረ መርቆኛል፤የመበለቲቱንም ልብ አሳርፌአለሁ።

14. ጽድቅን እንደ ልብስ ለበስሁ፤ፍትሕም መጐናጸፊያዬና ጥምጥሜ ነበር።

15. ለዕዉራን ዐይን፣ለአንካሶችም እግር ነበርሁ።

16. ለችግረኛው አባት፣ለባይተዋሩ ተሟጋች ነበርሁ።

17. የኀጢአተኛውን ክራንቻ ሰበርሁ፤የነጠቀውንም ከጥርሶቹ አስጣልሁ።

18. “እኔም በልቤ እንዲህ አልሁ፤ ‘ዘመኔ እንደ አሸዋ በዝቶ፣በቤቴ ተደላድዬ እሞታለሁ፤

ኢዮብ 29