ኢዮብ 29:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ኢዮብም እንዲህ ሲል ንግግሩን ቀጠለ፤

2. “በእግዚአብሔር የተጠበቅሁበትን ዘመን፣ያለፈውንም ወራት ምንኛ ተመኘሁ!

3. ያን ጊዜ መብራቱ በራሴ ላይ ይበራ ነበር፤በብርሃኑም በጨለማ ውስጥ ዐልፌ እሄድ ነበር፤

4. እኔም ብርቱ ነበርሁ፤የእግዚአብሔርም ወዳጅነት ቤቴን ይባርክ ነበር፤

5. ሁሉን የሚችል አምላክ ከእኔ ጋር ነበረ፤ልጆቼም በዙሪያዬ ነበሩ፤

6. መንገዴ በቅቤ የራሰ ነበር፤ዐለቱም የወይራ ዘይት ያመነጭልኝ ነበር።

ኢዮብ 29