ኢዮብ 28:23-28 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. ወደ እርሷ የሚወስደውን መንገድ የሚረዳ፣መኖሪያዋንም የሚያውቅ እግዚአብሔር ብቻ ነው፤

24. እርሱ የምድርን ዳርቻ ይመለከታልና፤ከሰማይ በታች ያለውንም ሁሉ ያያል።

25. ለነፋስ ኀይልን በሰጠ ጊዜ፣የውሆችን መጠን በለካ ጊዜ፣

26. ለዝናብ ሥርዐትን፣ለነጐድጓድም መንገድን ባበጀ ጊዜ፣

27. በዚያን ጊዜ ጥበብን ተመለከታት፤ ገመገማትም፤አጸናት፤ መረመራትም።

28. ከዚያም ሰውን፣‘እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብ ነው፤ከክፋትም መራቅ ማስተዋል ነው’ አለው።”

ኢዮብ 28