ኢዮብ 28:19-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. የኢትዮጵያ ቶጳዝዮን ሊስተካከላት አይችልም፤ዋጋዋም በንጹሕ ወርቅ አይተመንም።

20. “ታዲያ፣ ጥበብ ከወዴት ትመጣለች?ማስተዋልስ የት ትገኛለች?

21. ከሕያዋን ፍጥረታት ዐይን ሁሉ ተሰውራለች፤ከሰማይ ወፎችም ተሸሽጋለች።

22. ጥፋትና ሞት፣‘ወሬዋን ብቻ ሰማን’ ይላሉ።

23. ወደ እርሷ የሚወስደውን መንገድ የሚረዳ፣መኖሪያዋንም የሚያውቅ እግዚአብሔር ብቻ ነው፤

ኢዮብ 28