ኢዮብ 24:14-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. ቀኑ ሲመሽ፣ ነፍሰ ገዳይ ይነሣል፤ድኾችንና ችግረኞችን ይገድላል፤በሌሊትም እንደ ሌባ ያደባል፤

15. አመንዝራ በዐይኑ ድንግዝግዝታን ይጠባበቃል፤‘ማንም አያየኝም’ ብሎ ያስባል፤ፊቱንም ይሸፍናል።

16. በጨለማ፣ ቤት ሰርስረው ይገባሉ፤በቀን ግን ይሸሸጋሉ፤ብርሃንንም አይፈልጉም።

17. ድቅድቅ ጨለማ ለሁላቸው እንደ ንጋት ነው፤አሸባሪውን ጨለማ ይወዳጃሉ።

ኢዮብ 24