ኢዮብ 22:19-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. “ጻድቃንም የእነዚያን ጥፋት አይተው ይደሰታሉ፤ንጹሓንም እንዲህ ብለው ያፌዙባቸዋል፤

20. በእርግጥ ጠላቶቻችን ጠፍተዋል፤ሀብታቸውም በእሳት ተበልቶአል።’

21. “ለእግዚአብሔር ተገዛ፤ ከእርሱም ጋር ሰላም ይኑርህ፤በረከትም ታገኛለህ።

22. ምክርን ከአፉ ተቀበል፤ቃሉንም በልብህ አኑር።

23. ሁሉን ወደሚችል አምላክ ብትመለስ ትጠገናለህ፤ክፋትን ከድንኳንህ ብታርቅ፣

24. የወርቅህን አንኳር ትቢያ ላይ፣የኦፊር ወርቅህንም ጥልቅ ሸለቆ ውስጥ ብትጥለው፣

ኢዮብ 22