ኢዮብ 22:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ቴማናዊውም ኤልፋዝ እንዲህ ሲል መለሰ፤

2. “ሰው እግዚአብሔርን ሊጠቅም ይችላልን?ጠቢብ እንኳ ቢሆን ምን ይጠቅመዋል?

3. አንተ ጻድቅ ብትሆን ሁሉን የሚችለውን አምላክ ምን ደስ ታሰኘዋለህ?መንገድህ ያለ ነቀፋ ቢሆንስ የሚተርፈው ምንድን ነው?

4. “እርሱ የሚገሥጽህ፣ፍርድ ቤትም የሚያቀርብህ ስለምትፈራው ነውን?

5. ክፋትህ ታላቅ፣ኀጢአትህ ፍጻሜ የሌለው አይደለምን?

ኢዮብ 22