ኢዮብ 21:5-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. ተመልከቱኝና ተገረሙ፤አፋችሁን በእጃችሁ ለጒሙ።

6. ስለዚህ ነገር ባሰብሁ ቍጥር እደነግጣለሁ፤ሰውነቴም በፍርሀት ይንቀጠቀጣል።

7. ኀጢአተኞች ለምን በሕይወት ይኖራሉ?ለምን ለእርጅና ይበቃሉ? ለምንስ እያየሉ ይሄዳሉ?

8. ዘራቸው በዐይናቸው ፊት፣ልጆቻቸውም በዙሪያቸው ጸንተው ሲኖሩ ያያሉ፤

9. ቤታቸው ያለ ሥጋት በሰላም ይኖራል፤የእግዚአብሔርም በትር የለባቸውም።

ኢዮብ 21