ኢዮብ 21:30-33 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

30. ክፉ ሰው በመቅሠፍት ቀን እንደሚጠበቅ፣በቍጣም ቀን እንደሚተርፍ አታውቁምን?

31. ተግባሩን ፊት ለፊት የሚነግረው ማን ነው?የእጁንስ ማን ይሰጠዋል?

32. ወደ መቃብር ይወስዱታል፤ለመቃብሩም ጠባቂ ይደረግለታል።

33. የሸለቈው ዐፈር ምቹ ይሆንለታል፤ሰው ሁሉ ይከተለዋል፤ስፍር ቍጥር የሌለው ሕዝብ በፊቱ ይሄዳል።

ኢዮብ 21