ኢዮብ 21:12-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. በከበሮና በክራር ይዘፍናሉ፤በዋሽንትም ድምፅ ይፈነጫሉ።

13. ዕድሜያቸውን በተድላ ያሳልፋሉ፤በሰላምም ወደ መቃብር ይወርዳሉ።

14. እግዚአብሔርንም እንዲህ ይሉታል፤ ‘አትድረስብን!መንገድህንም ማወቅ አንፈልግም።

15. እናገለግለው ዘንድ፣ ሁሉን ቻይ አምላክ ማን ነው?ወደ እርሱ ብንጸልይስ ምን እናገኛለን?’

16. ይሁንና ብልጽግናቸው በእጃቸው አይደለም፤ከኀጢአተኞች ምክር እርቃለሁ።

ኢዮብ 21