5. ነገር ግን ራሳችሁን በእኔ ላይ ከፍ ብታደርጉ፣መዋረዴንም እኔን ለመሞገት ብትጠቀሙበት፣
6. እግዚአብሔር እንደ በደለኝ፣በመረቡም እንደ ከበበኝ ዕወቁ።
7. “ ‘ተበደልሁ’ ብዬ ብጮኽ ማንም አይመልስልኝም፤ድምፄን ከፍ አድርጌ ባሰማም፣ ፍትሕ አላገኝም።
8. እንዳላልፍ መንገዴን ዘግቶአል፤መሄጃዬንም በጨለማ ጋርዶአል።
9. ክብሬን ገፍፎኛል፤ዘውዴንም ከራሴ ላይ ወስዶአል።
10. እስክወገድ ድረስ በሁሉ አቅጣጫ አፈራርሶኛል፤ተስፋዬንም እንደ ዛፍ ነቅሎታል።