ኢዮብ 19:20-25 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

20. ቈዳና ዐጥንት ብቻ ሆኜ ቀረሁ፤ድድ ብቻ ቀርቶልኝ አመለጥሁ።

21. “ወዳጆቼ ሆይ፤ ራሩልኝ፤የእግዚአብሔር እጅ መታኛለችና ዕዘኑልኝ።

22. እግዚአብሔር እንዳሳደደኝ ለምን ታሳድዱኛላችሁ?አሁንም ሥጋዬ አልበቃችሁምን?

23. “ምነው ቃሌ በተጻፈ ኖሮ!በመጽሐፍም በታተመ!

24. ምነው በብረትና በእርሳስ በተጻፈ ኖሮ!በዐለትም ላይ በተቀረጸ!

25. የሚቤዠኝ ሕያው እንደሆነ፣በመጨረሻም በምድር ላይ እንደሚቆም ዐውቃለሁ።

ኢዮብ 19