ኢዮብ 19:2-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. “ነፍሴን የምታስጨንቋት፣በቃልስ የምትደቍሱኝ እስከ መቼ ነው?

3. እነሆ፤ ዐሥር ጊዜ ዘለፋችሁኝ፤ያለ ዕፍረትም በደላችሁኝ።

4. በእውነት ተሳስቼ ከሆነ፣ስሕተቱ የራሴ ጒዳይ ነው።

5. ነገር ግን ራሳችሁን በእኔ ላይ ከፍ ብታደርጉ፣መዋረዴንም እኔን ለመሞገት ብትጠቀሙበት፣

6. እግዚአብሔር እንደ በደለኝ፣በመረቡም እንደ ከበበኝ ዕወቁ።

7. “ ‘ተበደልሁ’ ብዬ ብጮኽ ማንም አይመልስልኝም፤ድምፄን ከፍ አድርጌ ባሰማም፣ ፍትሕ አላገኝም።

8. እንዳላልፍ መንገዴን ዘግቶአል፤መሄጃዬንም በጨለማ ጋርዶአል።

9. ክብሬን ገፍፎኛል፤ዘውዴንም ከራሴ ላይ ወስዶአል።

ኢዮብ 19