ኢዮብ 19:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ኢዮብም እንዲህ ሲል መለሰ፤

2. “ነፍሴን የምታስጨንቋት፣በቃልስ የምትደቍሱኝ እስከ መቼ ነው?

3. እነሆ፤ ዐሥር ጊዜ ዘለፋችሁኝ፤ያለ ዕፍረትም በደላችሁኝ።

4. በእውነት ተሳስቼ ከሆነ፣ስሕተቱ የራሴ ጒዳይ ነው።

ኢዮብ 19