ኢዮብ 18:7-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. የርምጃው ብርታት ይደክማል፤የገዛ ዕቅዱም ይጥለዋል።

8. እግሩ በወጥመድ ይያዛል፤በመረብም ይተበተባል።

9. አሽክላ ተረከዙን ይይዘዋል፤ወስፈንጥርም ያጣብቀዋል።

10. በምድር ላይ የሸምበቆ ገመድ፣በመንገዱም ላይ ወጥመድ በስውር ይቀመጥለታል።

11. ድንጋጤ በዙሪያው ያስፈራራዋል፤ተከትሎም ያሳድደዋል።

12. መቅሠፍት ሊውጠው ቀርቦአል፤ጥፋትም የእርሱን ውድቀት ይጠባበቃል።

13. ደዌ ቈዳውን ይበላል፤የሞት በኵርም ቅልጥሙን ይውጣል።

14. ተማምኖ ከሚኖርበት ድንኳን ይነቀላል፤ወደ ድንጋጤም ንጉሥ ይነዳል።

15. ድንኳኑ በእሳት ይያያዛል፤በመኖሪያውም ላይ ዲን ይበተናል።

16. ሥሩ ከታች ይደርቃል፤ቅርንጫፉም ከላይ ይረግፋል።

17. መታሰቢያው ከምድር ገጽ ይጠፋል፤ስሙም በአገር አይነሣም።

ኢዮብ 18