6. የድንኳኑ ብርሃን ይጨልማል፤መብራቱም በላዩ ይጠፋል፤
7. የርምጃው ብርታት ይደክማል፤የገዛ ዕቅዱም ይጥለዋል።
8. እግሩ በወጥመድ ይያዛል፤በመረብም ይተበተባል።
9. አሽክላ ተረከዙን ይይዘዋል፤ወስፈንጥርም ያጣብቀዋል።
10. በምድር ላይ የሸምበቆ ገመድ፣በመንገዱም ላይ ወጥመድ በስውር ይቀመጥለታል።
11. ድንጋጤ በዙሪያው ያስፈራራዋል፤ተከትሎም ያሳድደዋል።
12. መቅሠፍት ሊውጠው ቀርቦአል፤ጥፋትም የእርሱን ውድቀት ይጠባበቃል።
13. ደዌ ቈዳውን ይበላል፤የሞት በኵርም ቅልጥሙን ይውጣል።
14. ተማምኖ ከሚኖርበት ድንኳን ይነቀላል፤ወደ ድንጋጤም ንጉሥ ይነዳል።