ኢዮብ 18:14-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. ተማምኖ ከሚኖርበት ድንኳን ይነቀላል፤ወደ ድንጋጤም ንጉሥ ይነዳል።

15. ድንኳኑ በእሳት ይያያዛል፤በመኖሪያውም ላይ ዲን ይበተናል።

16. ሥሩ ከታች ይደርቃል፤ቅርንጫፉም ከላይ ይረግፋል።

17. መታሰቢያው ከምድር ገጽ ይጠፋል፤ስሙም በአገር አይነሣም።

18. ከብርሃን ወደ ጨለማ ይጣላል፤ከዓለምም ይወገዳል።

19. በሕዝቡ መካከል ልጅ ወይም ዘር አይኖረውም፤በኖረበትም አገር ተተኪ አያገኝም።

20. ባጋጠመው ሁኔታ የምዕራብ ሰዎች ይደነግጣሉ፤የምሥራቅም ሰዎች በፍርሀት ይዋጣሉ።

21. በርግጥ የክፉ ሰው መኖሪያ፣እግዚአብሔርንም የማያውቅ ሰው መድረሻ ይህ ነው።”

ኢዮብ 18