ኢዮብ 18:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ሹሐዊው በልዳዶስ እንዲህ ሲል መለሰ፤

2. “ይህን ንግግር የምትጨርሰው መቼ ነው?እስኪ ልብ ግዛ፤ ከዚያ በኋላ እንነጋገራለን።

3. ለምን እንደ ከብት መንጋ እንቈጠራለን?እንደ ደንቈሮስ ለምን ታየናለህ?

4. አንተ በቍጣ የነደድህ እንደሆነ፣ምድር ባዶዋን ትቀራለች?ወይስ ዐለት ከሥፍራው ተነቅሎ ይወሰዳል?

ኢዮብ 18