3. “እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ተያዥ ሁነኝ፤ከአንተ ሌላ ዋስ የሚሆነኝ ማን አለ?
4. እንዳያስተውሉ ልባቸውን ይዘሃል፤ስለዚህ ድል አትሰጣቸውም።
5. ለጥቅም ሲል ወዳጁን የሚያወግዝ፣የልጆቹ ዐይን ይታወራል።
6. “እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ መተረቻ፣ፊቱ ላይ የሚተፋበት ሰውም አደረገኝ።
7. ዐይኔ ከሐዘን የተነሣ ፈዘዘ፤መላ አካሌም እንደ ጥላ ሆነ።
8. ቅኖች በዚህ ነገር ይደነግጣሉ፤ንጹሓንም በዐመፀኞች ላይ ይነሣሉ።
9. ጻድቃን ግን በያዙት መንገድ ይጸናሉ፤ንጹሕ እጅ ያላቸውም እየበረቱ ይሄዳሉ።