ኢዮብ 15:9-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. እኛ የማናውቀው አንተ ግን የምታውቀው ምን ነገር አለ?እኛስ የሌለን አንተ ያለህ ማስተዋል የቱ ነው?

10. በዕድሜ ከአባትህ የሚበልጡ፣የሸበቱ ሽማግሌዎች ከእኛ ጋር አሉ።

11. የእግዚአብሔር ማጽናናት፣በርጋታ የተነገረህ ቃል አነሰህን?

12. ልብህ ለምን ይሸፍታል?ዐይንህንስ ምን ያጒረጠርጠዋል?

13. በእግዚአብሔር ላይ እንድትቈጣ፣እንደዚህ ያለ ቃል ከአፍህ እንዲወጣ ያደረገህ ምንድን ነው?

ኢዮብ 15