ኢዮብ 15:22-26 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

22. ከጨለማ ወጥቶ ማምለጥ ይፈራል፤ለሰይፍም የተመደበ ነው።

23. የአሞራ እራት ለመሆን ይቅበዘበዛል፤የጨለማ ቀን መቅረቡን ያውቃል።

24. ጭንቀትና ሐዘን ያስፈራሩታል፤ለማጥቃት እንደ ተዘጋጀ ንጉሥም ያይሉበታል፤

25. እጁን በእግዚአብሔር ላይ አንሥቶአልና፤ሁሉን የሚችለውን አምላክም ደፍሮአል፤

26. ወፍራምና ጠንካራ ጋሻ አንግቦ፣ሊቋቋመው ወጥቶአል።

ኢዮብ 15