ኢዮብ 15:14-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. “ንጹሕ ይሆን ዘንድ ሰው ምንድን ነው?ጻድቅስ ይሆን ዘንድ፣ ከሴት የተወለደ ምንድን ነው?

15. እነሆ፤ እግዚአብሔር በቅዱሳኑ እንኳ አይታመንም፤ሰማያትም በእርሱ ፊት ንጹሓን አይደሉም።

16. ታዲያ፣ ክፋትን እንደ ውሃ የሚጠጣ!አስጸያፊና ርኩስ ሰውማ እንዴት ይታመን!

17. “አድምጠኝ፤ በግልጽ አስረዳሃለሁ፤ያየሁትንም እነግርሃለሁ፤

18. ጠቢባን ከአባቶቻቸው የተቀበሉትን፤ሳይሸሽጉ የተናገሩትን አስረዳሃለሁ፤

ኢዮብ 15