ኢዮብ 14:9-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. የውሃ ሽታ ባገኘ ጊዜ ያቈጠቍጣል፤እንደ ተተከለም ችግኝ ቅርንጫፍ ያወጣል።

10. ሰው ግን ይሞታል፤ ክንዱንም ይንተራሳል፤ነፍሱም ትወጣለች፤ ከእንግዲህስ የት ይገኛል?

11. ውሃ ከባሕር ውስጥ እንደሚያልቅ፣የወንዝ ውሃም ጠፍቶ እንደሚደርቅ፣

12. እንደዚሁም ሰው ይተኛል ቀናም አይልም፤ሰማይ እስከሚያልፍ ድረስ አይነቃም፤ከእንቅልፉም አይነሣም።

13. “ምነው መቃብር ውስጥ በሰወርኸኝ!ቍጣህም እስከሚያልፍ በሸሸግኸኝ!ምነው ቀጠሮ ሰጥተህ፣ከዚያ በኋላ ባስታወስኸኝ!

14. ሰው ከሞተ በኋላ ተመልሶ በሕይወት ይኖራል?እድሳቴ እስከሚመጣ ድረስ፣ተጋድሎ የሞላበትን ዘመኔን ሁሉ እታገሣለሁ።

15. ትጠራኛለህ፤ እኔም እመልስልሃለሁ፤የእጅህንም ሥራ ትናፍቃለህ።

16. በዚያን ጊዜ በእርግጥ እርምጃዬን ትከታተላለህ፤ነገር ግን ኀጢአቴን አትቈጣጠርም።

17. መተላለፌ በከረጢት ይቋጠራል፤ኀጢአቴንም ትሸፍናለህ።

18. “ተራራ እንደሚሸረሸርና እንደሚወድቅ፣ዐለትም ከስፍራው እንደሚወገድ፣

19. ውሃ ድንጋይን እንደሚቦረቡር፣ጐርፍም ዐፈርን አጥቦ እንደሚወስድ፣አንተም የሰውን ተስፋ ታጠፋለህ።

ኢዮብ 14