ኢዮብ 13:8-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. ለእርሱ ታደላላችሁን?ለእግዚአብሔር ጥብቅና ልትቆሙ ነውን?

9. እርሱ ቢመረምራችሁ መልካም ነገር ይገኝባችኋልን?ሰውን እንደምታታልሉ፣ ልታታልሉት ትችላላችሁን?

10. በስውር አድልዎ ብታደርጉ፣በርግጥ እርሱ ይገሥጻችኋል።

11. ግርማው አያስደነግጣችሁምን?ክብሩስ አያስፈራችሁምን?

12. ምሳሌዎቻችሁ የዐመድ ምሳሌዎች ናቸው፣መከላከያችሁም የጭቃ ምሽግ ነው።

13. “ዝም በሉ፤ እኔ ልናገር፤የመጣው ይምጣብኝ።

14. ሥጋዬን በጥርሴ፣ሕይወቴንም በእጄ ለምን እይዛለሁ?

15. ቢገድለኝም እንኳ በእርሱ ተስፋ አደርጋለሁ፤ስለ መንገዴም ፊት ለፊት እከራከረዋለሁ።

16. ኀጢአተኛ በእርሱ ፊት መቅረብ ስለማይችል፤ይህ ድፍረቴ ለመዳኔ ይሆናል።

17. ቃሌን በጥንቃቄ አድምጡ፤እኔ የምለውንም ጆሮአችሁ በሚገባ ይስማ፤

18. እንግዲህ ጒዳዬን ይዤ ቀርቤአለሁ፤እንደሚፈርድልኝም ዐውቃለሁ።

ኢዮብ 13