ኢዮብ 12:15-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. እርሱ ውሃን ቢከለክል፣ ድርቅ ይሆናል፤ቢለቀውም ውሃው ምድሪቱን ያጥለቀልቃል።

16. ብርታትና ድል ማድረግ በእርሱ ዘንድ ይገኛል፤አታላዩም ተታላዩም በእርሱ እጅ ናቸው።

17. አማካሪዎችን ከጥበባቸው ያራቍታል፤ፈራጆችንም ማስተዋል ይነሣል።

18. ነገሥታትን ድግ ያስፈታል፤ገመድም በወገባቸው ያስራል።

19. ካህናትን ከክህነታቸው ያዋርዳል፤ለዘመናት የተደላደሉትንም ይገለብጣል።

ኢዮብ 12