ኢዮብ 11:5-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. ምነው እግዚአብሔር ቢናገርህ!ከንፈሩንም በአንተ ላይ ቢከፍት!

6. እውነተኛ ጥበብ ባለ ብዙ ፈርጅ ናትና፣የጥበብንም ምስጢር ምነው በገለጠልህ!እግዚአብሔር ለኀጢአትህ የሚገባውን እንዳላስከፈለህ ባወቅህ ነበር።

7. “የእግዚአብሔርን ጥልቅ ምስጢር ልትለካ ትችላለህን?ወይስ ሁሉን የሚችለውን አምላክ መርምረህ ትደርስበታለህን?

8. ከሰማይ ይልቅ ከፍ ይላል፤ ምን ልታደርግ ትችላለህ?ከሲኦልም ይጠልቃል፤ ምን ልታውቅ ትችላለህ?

9. መጠኑ ከምድር ይልቅ ይረዝማል፤ከባሕርም ይልቅ ይሰፋል።

10. “እርሱ ተከታትሎ መጥቶ በግዞት ቢያስቀምጥህ፣የፍርድ ሸንጎም ቢሰበስብ፣ ማን ሊከለክለው ይችላል?

11. በእውነት እርሱ ሸፍጠኞችን ያውቃል፣ክፋት ሲሠራም ልብ ይላል።

ኢዮብ 11