ኢዮብ 11:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ነዕማታዊው ሶፋር እንዲህ ሲል መለሰ፤

2. “ይህ ሁሉ ቃል መልስ ማግኘት አይገባውምን?ወይስ ተናጋሪ ሰው እንደ እውነተኛ ይቈጠርን?

3. በውኑ የአንተ መዘላበድ ሰውን ዝም ያሰኛልን?ስታፌዝስ የሚገሥጽህ የለም?

4. እግዚአብሔርንም፣ ‘ትምህርቴ የጠራ፤በዐይንህም ፊት የጸዳሁ ነኝ’ ትለዋለህ።

5. ምነው እግዚአብሔር ቢናገርህ!ከንፈሩንም በአንተ ላይ ቢከፍት!

ኢዮብ 11