ኢዮብ 10:9-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. እንደ ሸክላ እንዳበጀኸኝ አስብ፤አሁን ደግሞ ወደ ትቢያ ትመልሰኛለህን?

10. እንደ ወተት አላፈሰስኸኝምን?እንደ እርጎስ አላረጋኸኝምን?

11. ቈዳና ሥጋ አለበስኸኝ፤በዐጥንትና በጅማትም አገጣጥመህ ሠራኸኝ።

12. ሕይወትን ሰጠኸኝ፤ በጎነትንም አሳየኸኝ፤እንክብካቤህም መንፈሴን ጠበቀ።

ኢዮብ 10