ኢዮብ 10:6-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ታዲያ፣ በደልን የምትፈላልግብኝ፣ኀጢአቴንም የምትከታተለው ለምንድን ነው?

7. እኔ በደለኛ እንዳልሆንሁ፣ከእጅህም ሊያስጥለኝ ማንም እንደማይችል አንተ ታውቃለህ።

8. “እጅህ አበጀችኝ፤ ሠራችኝም፤መልሰህ ደግሞ ታጠፋኛለህን?

9. እንደ ሸክላ እንዳበጀኸኝ አስብ፤አሁን ደግሞ ወደ ትቢያ ትመልሰኛለህን?

10. እንደ ወተት አላፈሰስኸኝምን?እንደ እርጎስ አላረጋኸኝምን?

ኢዮብ 10