32. ስድስተኛው ዕጣ ለንፍታሌም ነገድ በየጐሣ በየጐሣው ወጣ፤
33. ድንበራቸውም ከሔሌፍና በጸዕነኒም ካለው ከትልቁ የወርካ ዛፍ ይነሣና በአዳ ሚኔቄብና በየብኒኤል አልፎ ወደ ለቁም በመምጣት ዮርዳኖስ ላይ ይቆማል፤
34. ድንበሩ በአዝኖት ታቦር ያልፍና ወደ ምዕራብ በመታጠፍ ሑቆቅ ላይ ይቆማል፤ ይኸው ድንበር በደቡብ ዛብሎንን፣ በምዕራብ አሴርን፣ በምሥራቅ ዮርዳኖስን ይነካል።
35. የተመሸጉትም ከተሞች እነዚህ ናቸው፤ ጺዲም፣ ጼር፣ ሐማት፣ ረቃት፣ ኬኔሬት፣
36. አዳማ፣ ራማ፣ አሶር፣
37. ቃዴስ፣ ኤድራይ፣ ዐይንሐጾር፣
38. ይርኦን፣ ሚግዳልኤል፣ ሖሬም፣ ቤትዓናትና ቤትሳሚስ። እነዚህ ከነ መንደሮቻቸው ዐሥራ ዘጠኝ ከተሞች ናቸው።
39. እነዚህ ለንፍታሌም ነገድ ርስት ሆነው በየጐሣው የተደለደሉ ከተሞችና መንደሮች ነበሩ።
40. ሰባተኛው ዕጣ ለዳን ነገድ በየጐሣው ወጣ፤
41. የወረሱትም ምድር የሚከተሉትን ያካትታል፤ጾርዓ፣ ኤሽታኦል፣ ዒርሼሜሽ፣
42. ሸዕለቢን፣ ኤሎን፣ ይትላ፣
43. ኤሎን፣ ተምና፣ አቃሮን፣
44. ኢልተቄ፣ ገባቶን፣ ባዕላት፣
45. ይሁድ፣ ብኔብረቅ፣ ጋትሪሞን፣
46. ሜያርቆንና በኢዮጴ ፊት ለፊት ያለው ርቆን።
47. ነገር ግን የዳን ዘሮች ርስታቸው አልበቃቸውም፣ ወደ ሌሼም ወጥተው አደጋ በመጣል ያዟት፤ ሰዎቹንም በሰይፍ ስለት ፈጅተው ይዞታቸው አደረጓት፤ በዚያው ሰፈሩ፤ ስሟንም ለውጠው በአባታቸው ስም ዳን አሏት።
48. እነዚህ ለዳን ነገድ ርስት ሆነው በየጐሣው የተደለደሉ ከተሞችና መንደሮች ነበሩ።
49. እስራኤላውያን ድርሻ ድርሻቸውን ከያዙ በኋላ፣ ለነዌ ልጅ ለኢያሱ በመካከላቸው ርስት ሰጡት፤
50. እግዚአብሔር ባዘዘውም መሠረት በኰረብታማው የኤፍሬም ምድር የምትገኘውን ተምናሴራ የምትባለውን የፈለጋትን ከተማ ሰጡት፤ እርሱም ከተማዪቱን ሠራ፤ መኖሪያውም አደረጋት።
51. እንግዲህ ካህኑ አልዓዛር፣ የነዌ ልጅ ኢያሱና የእስራኤል ነገድ የየጐሣ መሪዎች ሴሎ ላይ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ፣ በእግዚአብሔር ፊት ዕጣ ያደላደሉት ርስት ይህ ነው፤ የምድሪቱንም አከፋፈል በዚህ ሁኔታ ፈጸሙ።