29. ድንበሩ ወደ ራማ ከዞረ በኋላ ወደ ተመሸገው ወደ ጢሮስ ከተማ ታጥፎ ወደ ሖሳ ይመለስና በአክዚብ በኩል ሜድትራኒያን ባሕር ደርሶ ይቆማል፤
30. ይህም የዑማን፣ የአፌቅንና የረአብን ምድር ይጨምራል። በዚህም ሃያ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው ይገኛሉ።
31. እነዚህ ለአሴር ነገድ ሆነው በየጐሣው የተደለደሉ ከተሞችና መንደሮቻቸው ነበሩ።
32. ስድስተኛው ዕጣ ለንፍታሌም ነገድ በየጐሣ በየጐሣው ወጣ፤
33. ድንበራቸውም ከሔሌፍና በጸዕነኒም ካለው ከትልቁ የወርካ ዛፍ ይነሣና በአዳ ሚኔቄብና በየብኒኤል አልፎ ወደ ለቁም በመምጣት ዮርዳኖስ ላይ ይቆማል፤
34. ድንበሩ በአዝኖት ታቦር ያልፍና ወደ ምዕራብ በመታጠፍ ሑቆቅ ላይ ይቆማል፤ ይኸው ድንበር በደቡብ ዛብሎንን፣ በምዕራብ አሴርን፣ በምሥራቅ ዮርዳኖስን ይነካል።
35. የተመሸጉትም ከተሞች እነዚህ ናቸው፤ ጺዲም፣ ጼር፣ ሐማት፣ ረቃት፣ ኬኔሬት፣
36. አዳማ፣ ራማ፣ አሶር፣
37. ቃዴስ፣ ኤድራይ፣ ዐይንሐጾር፣
38. ይርኦን፣ ሚግዳልኤል፣ ሖሬም፣ ቤትዓናትና ቤትሳሚስ። እነዚህ ከነ መንደሮቻቸው ዐሥራ ዘጠኝ ከተሞች ናቸው።
39. እነዚህ ለንፍታሌም ነገድ ርስት ሆነው በየጐሣው የተደለደሉ ከተሞችና መንደሮች ነበሩ።
40. ሰባተኛው ዕጣ ለዳን ነገድ በየጐሣው ወጣ፤