ኢያሱ 19:23-40 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. እነዚህ ለይሳኮር ነገድ ርስት ሆነው ለየጐሣ ለየጐሣው የተደለደሉ ከተሞችና መንደሮቻቸው ነበሩ።

24. አምስተኛ ዕጣ ለአሴር ነገድ በየጐሣ በየጐሣው ወጣ፤

25. ምድራቸውም የሚከተሉትን ያካትታል፤ሔልቃት፣ ሐሊ፤ ቤጤን፣ አዚፍ፣

26. አላሜሌክ፣ ዓምዓድ እንዲሁም ሚሽአል። ድንበሩ በስተ ምዕራብ ቀርሜሎስንና ሺሖርሊብናትን ይነካል፣

27. ከዚያም በምሥራቅ በኩል ወደ ቤትዳጎን ይመለስና ዛብሎንንና የይፍታሕኤልን ሸለቆ ይዞ ካቡልን በስተ ግራ በመተው በሰሜን በኩል ወደ ቤትዔሜቅና ወደ ንዒኤል ይቃናል።

28. በመቀጠልም ወደ ዔብሮን፣ ወደ ረአብ፣ እንዲሁም ወደ ሐሞንና ወደ ቃና ሽቅብ ወጥቶ እስከ ታላቁ ሲዶና ይደርሳል።

29. ድንበሩ ወደ ራማ ከዞረ በኋላ ወደ ተመሸገው ወደ ጢሮስ ከተማ ታጥፎ ወደ ሖሳ ይመለስና በአክዚብ በኩል ሜድትራኒያን ባሕር ደርሶ ይቆማል፤

30. ይህም የዑማን፣ የአፌቅንና የረአብን ምድር ይጨምራል። በዚህም ሃያ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው ይገኛሉ።

31. እነዚህ ለአሴር ነገድ ሆነው በየጐሣው የተደለደሉ ከተሞችና መንደሮቻቸው ነበሩ።

32. ስድስተኛው ዕጣ ለንፍታሌም ነገድ በየጐሣ በየጐሣው ወጣ፤

33. ድንበራቸውም ከሔሌፍና በጸዕነኒም ካለው ከትልቁ የወርካ ዛፍ ይነሣና በአዳ ሚኔቄብና በየብኒኤል አልፎ ወደ ለቁም በመምጣት ዮርዳኖስ ላይ ይቆማል፤

34. ድንበሩ በአዝኖት ታቦር ያልፍና ወደ ምዕራብ በመታጠፍ ሑቆቅ ላይ ይቆማል፤ ይኸው ድንበር በደቡብ ዛብሎንን፣ በምዕራብ አሴርን፣ በምሥራቅ ዮርዳኖስን ይነካል።

35. የተመሸጉትም ከተሞች እነዚህ ናቸው፤ ጺዲም፣ ጼር፣ ሐማት፣ ረቃት፣ ኬኔሬት፣

36. አዳማ፣ ራማ፣ አሶር፣

37. ቃዴስ፣ ኤድራይ፣ ዐይንሐጾር፣

38. ይርኦን፣ ሚግዳልኤል፣ ሖሬም፣ ቤትዓናትና ቤትሳሚስ። እነዚህ ከነ መንደሮቻቸው ዐሥራ ዘጠኝ ከተሞች ናቸው።

39. እነዚህ ለንፍታሌም ነገድ ርስት ሆነው በየጐሣው የተደለደሉ ከተሞችና መንደሮች ነበሩ።

40. ሰባተኛው ዕጣ ለዳን ነገድ በየጐሣው ወጣ፤

ኢያሱ 19