10. ሦስተኛው ዕጣ ለዛብሎን ነገድ በየጐሣ በየጐሣው ወጣ፤የርስታቸውም ድንበር እስከ ሣሪድ ይደርሳል፤
11. ወደ ምዕራብም በመሄድ በመርዓላ በኩል ያልፋል፤ ደባሼትን ተጠግቶም በዮቅንዓም አጠገብ እስካለው ወንዝ ድረስ ይዘልቃል።
12. ከሣሪድም ወደ ምሥራቅ በመታጠፍ፣ የፀሓይ መውጫ ወደ ሆነው አገር ወደ ኪስሎትታቦር በመዝለቅ እስከ ዳብራት ሄዶ ወደ ያፊዓ ያቀናል፤
13. ከዚያም ወደ ምሥራቅ በመቀጠል፣ ወደ ጋትሔፍርና ወደ ዒትቃጺን ይዘልቃል፤ ከዚያ ደግሞ ወደ ሪሞን በመሄድ፣ ወደ ኒዓ ይታጠፋል።
14. በስተ ሰሜንም በኩል ወደ ሐናቶን ይዞርና በይፍታሕኤል ሸለቆ ላይ ይቆማል።
15. ደግሞም ቀጣትን፣ ነህላልን፣ ሺምሮንን፣ ይዳላንና ቤተ ልሔምን ይጨምራል፤ እነዚህም ከነ መንደሮቻቸው ዐሥራ ሁለት ከተሞች ናቸው።
16. እነዚህ ሁሉ ለዛብሎን ነገድ ርስት ሆነው ለየጐሣ ለየጐሣው የተደለደሉ ከተሞችና መንደሮቻቸው ነበሩ።
17. አራተኛው ዕጣ ለይሳኮር ነገድ በየጐሣ በየጐሣው ወጣ፤
18. ምድራቸውም የሚከተሉትን ያካትታል፤ኢይዝራኤል፣ ከስሎት፣ ሱነም፣
19. ሐፍራይም፣ ሺኦን፣ አናሐራት፣