ይኸው ድንበር ከራፋይም ሸለቆ በስተ ሰሜን ባለው በሄኖም ሸለቆ ትይዩ ቊልቊል ወደ ኰረብታው ግርጌ ይወርዳል፤ ከዚያም ከኢያቡሳውያን ከተማ በደቡብ በኩል ባለው ተረተር አድርጎ ወደ ሄኖም ሸለቆ በመውረድ እስከ ዓይንሮጌል ይዘልቃል።