51. ጎሶም፣ ሖሎንና ጊሎ፤ እነዚህም ዐሥራ አንዱ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።
52. አራብ፣ ዱማ፣ ኤሽዓን፣
53. ያኒም፣ ቤትታጱዋ፣ አፌቃ
54. ሑምጣ፣ ኬብሮን የተባለችው ቂርያትአርባቅና ጺዖር ናቸው፤ እነዚህም ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።
55. ማዖን፣ ቀርሜሎስ፣ ዚፍ፣ ዩጣ
56. ኢይዝራኤል፣ ዮቅድዓም፣ ዛኖዋሕ፣
57. ቃይን፣ ጊብዓና ተምና ናቸው፤ እነዚህም ዐሥር ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።
58. ሐልሑል፣ ቤትጹር፣ ጌዶር፣
59. ማዕራት፣ ቤትዓኖትና ኤልትቆን ናቸው፤ እነዚህም ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።
60. ቂርያትይዓሪም የተባለችው ቂርያ ትበኣልና ረባት፤ እነዚህም ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።
61. በምድረ በዳው ደግሞ እነዚህ ናቸው፤ ቤትዓረባ፣ ሚዲን፣ ስካካ፣
62. ኒብሻን፣ የጨው ከተማና ዓይንጋዲ፤ እነዚህም ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።
63. ነገር ግን የይሁዳ ዘሮች በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሳውያን ከቦታቸው ሊያስለቅቋቸው አልቻሉም፤ ኢያቡሳውያንም እስከ ዛሬ ድረስ ከይሁዳ ሕዝብ ጋር በኢየሩሳሌም አብረው ይኖራሉ።