ኢያሱ 15:19-29 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. እርስዋም፣ “እባክህ፤ በጎ ነገር አድርግልኝ፤ በኔጌብ መሬት እንደ ሰጠኸኝ ሁሉ፣ አሁንም የውሃ ምንጭ ጉድጓዶች ስጠኝ” አለችው፤ ካሌብም የላይኛውንና የታችኛውን ምንጮች ሰጣት።

20. ለይሁዳ ነገድ በየጐሣቸው የተሰጣቸው ርስት ይህ ነው፤

21. በኔጌብ አካባቢ በኤዶም ድንበር ላይ በወሰኑ ጫፍ የሚገኙት የይሁዳ ነገድ ደቡባዊ ከተሞች እነዚህ ነበሩ፤ቀብስኤል፣ ዔዴር፣ ያጉር፣

22. ቂና፣ ዲሞና፣ ዓድዓዳ፣

23. ቃዴስ፣ ሐጾር፤ ዩትናን፣

24. ዚፍ፣ ጤሌም፣ በዓሎት፣

25. ሐጾርሐዳታ፣ ሐጾር የምትባለው ቂርያትሐጾር

26. አማም፣ ሽማዕ፣ ሞላዳ፣

27. ሐጻርጋዳ፣ ሐሽሞን፣ ቤትጳሌጥ፣

28. ሐጸር ሹዓል፣ ቤርሳቤህ፣ ቢዝዮትያ

29. በኣላ፣ ዒዪም፣ ዓጼም፣

ኢያሱ 15