1. ለይሁዳ ነገድ በየጐሣቸው በዕጣ የተመደበው ድርሻ እስከ ኤዶም ምድር የሚወርድ ሲሆን፣ በስተ ደቡብ መጨረሻ እስከ ጺን ምድረ በዳ ድረስ ይዘልቃል።
2. የደቡብ ወሰናቸው፣ ከጨው ባሕር ደቡባዊ ጫፍ ካለው የባሕር ወሽመጥ ይነሣል፤
3. ከዚያም የአቅረቢምን መተላለፊያ በማቋረጥ በጺን በኩል እስከ ቃዴስ በርኔ ደቡባዊ ክፍል ይደርሳል፤ ደግሞም ሐጽሮንን አልፎ ወደ አዳር ይወጣና ወደ ቀርቃ ይታጠፋል፤