ኢያሱ 14:13-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. ከዚያም ኢያሱ የዮፎኒን ልጅ ካሌብን ባረከው፤ ኬብሮንንም ርስት አድርጎ ሰጠው።

14. ስለዚህም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ኬብሮን የቄኔዛዊው የዮፎኒ ልጅ የካሌብ ርስት ሆነች፤ የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡ ተከትሎአልና።

15. ኬብሮን ቀድሞ ከዔናቃውያን ሁሉ ታላቅ በሆነው በአርባቅ ስም ቂርያት አርባቅ ተብላ ትጠራ ነበር።ከዚያም ምድሪቱ ከጦርነት ዐረፈች።

ኢያሱ 14