ኢዩኤል 1:4-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ከአንበጣ መንጋ የተረፈውን፣ትልልቁ አንበጣ በላው፤ከትልልቁ አንበጣ የተረፈውን፣ኵብኵባ በላው፤ከኵብኵባ የተረፈውን፣ሌሎች አንበጦች በሉት።

5. እናንት ሰካራሞች፤ ተነሡ፤ አልቅሱ፤እናንት የወይን ጠጅ ጠጪዎች ሁሉ፤ ዋይ በሉ፤ስለ አዲሱ የወይን ጠጅ ዋይ ብላችሁ አልቅሱ፤አፋችሁ ላይ እንዳለ ተነጥቃችኋልና።

6. ኀያልና ቊጥር ስፍር የሌለው ሕዝብ፣ምድሬን ወሮአታልና፤ጥርሱ እንደ አንበሳ ጥርስ፣መንጋጋውም እንደ እንስት አንበሳ መንጋጋ ነው።

ኢዩኤል 1