ኢዩኤል 1:15-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. ወዮ ለዚያ ቀን፤ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና፤ሁሉን ከሚችል አምላክ እንደ ጥፋት ይመጣል።

16. የሚበላ ምግብ፣ከዐይናችን ፊት፣ደስታና ተድላ፣ከአምላካችን ቤት አልተቋረጠብንምን?

17. ዘሩ በዐፈር ውስጥ፣በስብሶ ቀርቶአል፤ግምጃ ቤቶቹ ፈራርሰዋል፤ጐተራዎቹም ተሰባብረዋል፤እህሉ ደርቆአልና።

18. መንጎች እንደ ምን ጮኹ፣ከብቶቹ ተደናግጠዋል፤መሰማሪያ የላቸውምና፤የበግ መንጎች እንኳ ተቸግረዋል።

ኢዩኤል 1