ኢሳይያስ 9:4-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ምድያም ድል በተመታ ጊዜ እንደሆነው፣የከበዳቸውን ቀንበር፣በትከሻቸው ላይ የነበረውን በትር፣የተጨቈኑበትንም ዘንግ ሰብረህላቸዋል።

5. የጦረኞች ጫማ ሁሉ፣በደም የተለወሰ ልብስም ሁሉ፣ለእሳት ይዳረጋል፤ይማገዳልም።

6. ሕፃን ተወልዶልናልና፤ወንድ ልጅ ተሰጥቶናል፤አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል።ስሙም፣ ድንቅ መካር፣ኀያል አምላክ፣የዘላለም አባት፣ የሰላም ልዑል ይባላል።

ኢሳይያስ 9