3. ሕዝብን አበዛህ፤ደስታቸውንም ጨመርህ፤ሰዎች ምርትን ሲሰበስቡ፣ምርኮንም ሲከፋፈሉደስ እንደሚላቸው ሁሉ፣እነርሱም በፊትህ ደስ ይላቸዋል።
4. ምድያም ድል በተመታ ጊዜ እንደሆነው፣የከበዳቸውን ቀንበር፣በትከሻቸው ላይ የነበረውን በትር፣የተጨቈኑበትንም ዘንግ ሰብረህላቸዋል።
5. የጦረኞች ጫማ ሁሉ፣በደም የተለወሰ ልብስም ሁሉ፣ለእሳት ይዳረጋል፤ይማገዳልም።
6. ሕፃን ተወልዶልናልና፤ወንድ ልጅ ተሰጥቶናል፤አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል።ስሙም፣ ድንቅ መካር፣ኀያል አምላክ፣የዘላለም አባት፣ የሰላም ልዑል ይባላል።
7. ለመንግሥቱ ስፋት፣ለሰላሙም ብዛት ፍጻሜ የለውም፤ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም፣መንግሥቱን በፍትሕና በጽድቅ ይመሠርታል፤ደግፎ በመያዝም ያጸናዋል።በዳዊት ዙፋን ይቀመጣል፤አገሩንም ሁሉ ይገዛል፤የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ቅናትይህን ያደርጋል።
8. ጌታ በያዕቆብ ላይ ቃል ላከ፤በእስራኤልም ላይ ይወድቃል።