ኢሳይያስ 9:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ነገር ግን ተጨንቀው የነበሩ ከእንግዲህ ተስፋ ቢስ አይሆኑም። በቀደመው ዘመን የዛብሎንንና የንፍታሌምን ምድር አዋረደ፤ በሚመጣው ዘመን ግን ከዮርዳኖስ ማዶ፣ በባሕር መንገድ አጠገብ ያለውን የአሕዛብን ገሊላ ያከብራል፤

2. በጨለማ የሚኖር ሕዝብታላቅ ብርሃን አየ፤በሞት ጥላ ምድር ለኖሩትምብርሃን ወጣላቸው።

3. ሕዝብን አበዛህ፤ደስታቸውንም ጨመርህ፤ሰዎች ምርትን ሲሰበስቡ፣ምርኮንም ሲከፋፈሉደስ እንደሚላቸው ሁሉ፣እነርሱም በፊትህ ደስ ይላቸዋል።

4. ምድያም ድል በተመታ ጊዜ እንደሆነው፣የከበዳቸውን ቀንበር፣በትከሻቸው ላይ የነበረውን በትር፣የተጨቈኑበትንም ዘንግ ሰብረህላቸዋል።

5. የጦረኞች ጫማ ሁሉ፣በደም የተለወሰ ልብስም ሁሉ፣ለእሳት ይዳረጋል፤ይማገዳልም።

6. ሕፃን ተወልዶልናልና፤ወንድ ልጅ ተሰጥቶናል፤አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል።ስሙም፣ ድንቅ መካር፣ኀያል አምላክ፣የዘላለም አባት፣ የሰላም ልዑል ይባላል።

ኢሳይያስ 9