2. እኔም፣ ካህኑን ኡሪያንንና የበራክዩን ልጅ ዘካርያስን ታማኝ ምስክሮቼ እንዲሆኑ እጠራቸዋለሁ።”
3. እኔም ወደ ነቢዪቱ ሄድሁ፤ እርሷም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች። እግዚአብሔርም፣ እንዲህ አለኝ፤ “ስሙን ማኸር-ሻላል-ሃሽ-ባዝ ብለህ ጥራው።
4. ሕፃኑም፣ ‘አባባ’ ወይም ‘እማማ’ ብሎ መጥራት ከመቻሉ በፊት፣ የደማስቆ ሀብትና የሰማርያ ምርኮ በአሦር ንጉሥ ይወሰዳል።”
5. እግዚአብሔርም እንደ ገና እንዲህ ሲል ተናገረኝ፤
6. “ይህ ሕዝብ በጸጥታ የሚፈሰውንየሰሊሆምን ውሆች ትቶ፣በረአሶንናበሮሜልዩ ልጅ ተደስቶአልና።