ኢሳይያስ 8:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፤ “ትልቅ ሰሌዳ ወስደህ፣ ‘ማኸር-ሻላል-ሃሽ-ባዝ’ ብለህ በተለመደው በሰው ፊደል ጻፍበት።

2. እኔም፣ ካህኑን ኡሪያንንና የበራክዩን ልጅ ዘካርያስን ታማኝ ምስክሮቼ እንዲሆኑ እጠራቸዋለሁ።”

3. እኔም ወደ ነቢዪቱ ሄድሁ፤ እርሷም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች። እግዚአብሔርም፣ እንዲህ አለኝ፤ “ስሙን ማኸር-ሻላል-ሃሽ-ባዝ ብለህ ጥራው።

4. ሕፃኑም፣ ‘አባባ’ ወይም ‘እማማ’ ብሎ መጥራት ከመቻሉ በፊት፣ የደማስቆ ሀብትና የሰማርያ ምርኮ በአሦር ንጉሥ ይወሰዳል።”

5. እግዚአብሔርም እንደ ገና እንዲህ ሲል ተናገረኝ፤

6. “ይህ ሕዝብ በጸጥታ የሚፈሰውንየሰሊሆምን ውሆች ትቶ፣በረአሶንናበሮሜልዩ ልጅ ተደስቶአልና።

7. ስለዚህ ጌታ ታላቁንና ብርቱውንየጐርፍ ውሃ፣የአሦርን ንጉሥ ከነግርማ ሞገሱ ሁሉ ያመጣባቸዋል።ውሃውም ከቦዩ ዐልፎ ተርፎበወንዙ ዳር ያለውን ምድር ሁሉ ያጥለቀልቃል፤

ኢሳይያስ 8