ኢሳይያስ 65:23-25 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. ድካማቸው በከንቱ አይቀርም፤ዕድለ ቢስ ልጆችም አይወልዱም፤እነርሱና ዘራቸው፣ እግዚአብሔር የባረከው ሕዝብ ይሆናሉ።

24. ገና ሳይጣሩ እመልስላቸዋለሁ፤ተናግረው ሳይጨርሱ እሰማለሁ።

25. ተኵላና የበግ ጠቦት በአንድነት ይበላሉ፤አንበሳ እንደ በሬ ሣር ይበላል፤እባብ ትቢያ ይልሳል፤በተቀደሰው ተራራዬም፣ጒዳት አያደርሱም፤ ጥፋት አያመጡም፤”ይላል እግዚአብሔር።

ኢሳይያስ 65