6. የግመል መንጋ፣የምድያምና የጌፌር ግልገል ግመሎችምድርሽን ይሞላሉ፤ወርቅና ዕጣን ይዘው፣ የእግዚአብሔርን ምስጋና እያወጁ፣ሁሉም ከሳባ ይመጣሉ።
7. የቄዳር የበግ መንጋ ሁሉ ወደ አንቺ ይሰበሰባል፤የነባዮት አውራ በጎች ያገለግሉሻል።እነዚህም በመሠዊያዬ ላይ ተቀባይነት የሚኖራቸው መሥዋዕቶች ይሆናሉ፤እኔም የክብር መቅደሴን ግርማ አጐናጽፈዋለሁ።
8. “ርግቦች ወደ ጐጆአቸው እንደሚበሩ፣እንደ ደመና የሚጓዙ እነዚህ እነማን ናቸው?
9. በርግጥ ደሴቶች እኔን ተስፋ ያደርጋሉ፤እርሱ ክብሩን ስላጐናጸፈሽ፣ለእስራኤል ቅዱስ፣ ለእግዚአብሔር አምላክሽ ክብር፣ከሩቅ ወንዶች ልጆችሽን፣ከነብራቸውና ከነወርቃቸው ለማምጣት፣የተርሴስ መርከቦች ቀድመው ይወጣሉ።
10. “ባዕዳን ቅጥሮችሽን ይሠራሉ፤ነገሥታቶቻቸው ያገለግሉሻል፤በቊጣዬ ብመታሽም፣ርኅራኄዬን በፍቅር አሳይሻለሁ።