1. “ብርሃንሽ መጥቶአልና ተነሺ አብሪ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ወጥቶልሻል።
2. እነሆ፤ ጨለማ ምድርን፣ድቅድቅ ጨለማም ሕዝቦችን ይሸፍናል፤ነገር ግን እግዚአብሔር ወጥቶልሻል፤ክብሩንም ይገልጥልሻል።
3. ሕዝቦች ወደ ብርሃንሽ፣ነገሥታትም ወደ ንጋትሽ ጸዳል ይመጣሉ።
4. “ቀና በዪ፤ ዙሪያሽን ተመልከቺ፤ሁሉም ተሰብስበው ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ወንዶች ልጆችሽ ከሩቅ፣ሴቶች ልጆችሽም በዕቅፍ ወደ አንቺ ይመጣሉ።
5. ከዚያም ታያለሽ፤ ታብረቀርቂያለሽ፤ልብሽ ይዘላል፤ በደስታም ይሞላል።በባሕሮች ያለው ሀብት ወደ አንቺ ይመጣል፤የነገሥታትም ብልጥግና የአንቺ ይሆናል።
6. የግመል መንጋ፣የምድያምና የጌፌር ግልገል ግመሎችምድርሽን ይሞላሉ፤ወርቅና ዕጣን ይዘው፣ የእግዚአብሔርን ምስጋና እያወጁ፣ሁሉም ከሳባ ይመጣሉ።
7. የቄዳር የበግ መንጋ ሁሉ ወደ አንቺ ይሰበሰባል፤የነባዮት አውራ በጎች ያገለግሉሻል።እነዚህም በመሠዊያዬ ላይ ተቀባይነት የሚኖራቸው መሥዋዕቶች ይሆናሉ፤እኔም የክብር መቅደሴን ግርማ አጐናጽፈዋለሁ።